Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለው…

June 26, 2024
ሚኒስቴሩ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል። በዚህም ሁለቱ ተቋማት በክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሙያ ደህንነትና ጤንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። ይህ ትብብር ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቁና በቂ ባለሙያዎችን በማቅረብ፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነትን በማረጋገጥ እንዲሁም ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት በመፍጠርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዘርፉ የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን ማሳካት የሚያስችል እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተመላክቷል። በተለይ በሚኒስቴሩ በልጽጎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የኢትየጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓትን ከኮርፖሬሽኑ የሥራ ባህሪ ጋር አጣጥሞ መጠቀም እንደሚያስፈልም የተጠቆመ ሲሆን ተቋማቱ በትትብብር የሚሠሩ ዝርዝር ሥራዎችን የለየ የጋራ ዕቅድ አቅዶ ወደ ሥራ ለመግባት ተስማምተዋል።
en_USEN
Scroll to Top