Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነት አስተሳስሮ እየሠራ ያለበት መንገድ የሚደነቅ ነው፡፡ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ

January 4, 2025
ሚኒስቴሩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነት አስተሳስሮ እየሠራ ያለበት መንገድ የሚደነቅ ነው፡፡ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የተመራ የምክር ቤቱ ጉዳዮች አማካሪና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሠው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ምልከታ አድርገዋል፡፡ በምልከታው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በተጠሪ ተቋማቱ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ታይተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባለፉት ሦስት ዓመታት ሚኒስቴሩ ያከናወናቸውን የሪፎርም ሥራዎች አስመልክተው ለምክር ቤቱ ኮሚቴ አባላት ማብራርያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሚኒስቴሩ እጅግ ባጠረ ጊዜ ውስጥ የተበታተነውን የሰው ሀይልና ሀብት አደራጅቶ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን ጠቁመው ለዚህም በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጠራን፣ ጥራትንና ፍጥነትን አስተሳስሮ እየሠራ ያለው ሥራ ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡ በጉብኝቱ የታዩት ሥራዎች ብልጽግናን እውን ለማድረግ የተቀመጡ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች እየተተገበሩ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የጠቆሙት የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ ምክር ቤቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ በሚያስፈልገው ጉዳች ላይ ለማገዝ ግንዛቤ እንዲኖረው ያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top