Mols.gov.et

መድረኩ ያሉንን ጠንካራ ጎኖችን የለየንበት እና ጉድለቶቻችንን ለማረም በጋራ የተግባባንበት ነው።

February 12, 2024
“መድረኩ ያሉንን ጠንካራ ጎኖችን የለየንበት እና ጉድለቶቻችንን ለማረም በጋራ የተግባባንበት ነው።” ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ሥራ በክህሎት ይመራ!” በሚል መሪ ሀሳብ ከክልሎች፣ ተጠሪ ተቋማቱ፣ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በሠመራ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የመጀመሪያውን ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የምክክር መድረክ አጠናቋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስተቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለፁት፣ መድረኩ በሥራ ስምሪት፣ በክህሎት ልማት እና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ያሉ ጠንካራ ጎኖች የለየንበት እና ያሉ ጉድለቶችንም ለማረም የተግባባንበት ስኬታማ መድረክ ነው። ሥራ በክህሎት እንዲመራ በተጀመረው ከፍተኛ ጥረት በርካታ ዜጎች ሰልጥነው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው በቀሪ ወራት በሶስቱም ዘርፍ ቀሪ ስራዎቻችን ማሳካት በሚያስችል መልኩ መረባረብ ይገባል ብለዋል። የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፣ በጀት ዓመቱ አበረታች ስራዎች የተተገበሩበት እንደነበር ገልጸው የስልጠና ጥራት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በመገንዘብ በልዩ ትኩረት ልንመራው ይገባል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ እንደገለጹት በየደረጃው በእቅድ የተግባባንባቸው ስራዎች የሚገኙበት ደረጃ ለማየት ሀገር አቀፍ የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ድጋፍና ክትትል አድርጓል። በዚህም በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸውን በድጋፍና ክትትሉ መረጋገጡን ገልጸው በጉድለት የታዩ ጉዳዮች ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚወርድ ጠቁመዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በርካታ ልምድና ተሞክሮ ያገኙበትና ለቀጣይ ሥራዎች መግባባት የፈጠሩበት መሆኑን ጠቁመው በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛው ዘርፍ ላይ ሊሻሻሉ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እድሳት ላይ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላት እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
en_USEN
Scroll to Top