Mols.gov.et

“መድረኩ ምቹ፣ ዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና…

December 6, 2023
“መድረኩ ምቹ፣ ዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ እንዲረጋገጥ በርካታ ግብዓት ያገኘንበት መድረክ ነው፡፡” ክቡር ዶ/ር አሰግድ ጌታቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴአታ “ማህበራዊ ምክክርና የላቀ ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበት አንድ መቶኛ ዓመትና የ2016 የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ የማጠቃለያና የዕውቅና መስጫ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አሰግድ ጌታቸው እንደገለጹት፤ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደው መድረክ ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር፣ ምምትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የአሰሪና ሠራተኛ ማህበራትን ማጠናከር፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት አገልግሎትን ማስፋት፣ የማህበራዊ ምክክርን ማላቅ፣ የስደተኛ ሠራተኞችን መብትና ደህንነት ማስጠበቅ፣ የሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትና ማጠናከር እና የሦስትዮሽ ውይይት እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛውን የመደራጀት ምጣኔን ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ በዚህም መድረኩ ምቹ፣ ዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ እንዲረጋገጥ በርካታ ግብዓት ያገኘንበት የተሳካ መድረክ ነው ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top