Mols.gov.et

መንግስት ለዲጂታል ኢንዱስትሪ ልማት የሰጠው ትኩረት…

December 21, 2023
“መንግስት ለዲጂታል ኢንዱስትሪ ልማት የሰጠው ትኩረት ኢትዮጵያ በዘርፉ ተጠቃሚ እና ተወዳዳሪ እንድትሆን የማድረግ አቅም አለው፡፡” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በዲጂታል ኢንዱስትሪ አውትሶርስ ተደርገው በሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የሚመክር መድረክ በዘርፉ የተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ በዲጂታል ኢንዱስትሪ የአውትሶርሲንግ ሥራ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር እና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ በመሆኑ መንግስትም ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ ዘርፍ በተጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስታውሰው ዘርፉ ካለው ሰፊ ዕድል አኳያ ገና ያልተነካና ለሀገራችን በርካታ ዕድሎችን ይዞ የመጣ ነው ብለዋል፡፡ መንግስት በዘርፉ በትኩረት እያከናወናቸው የሚገኙት አይሲቲ ፓርኮች ልማት፣ የመረጃ ማዕከሎች ግንባታ፣ የቴሌኮም አገልግሎቶች እና የመሳሰሉት መሰረት ልማቶች በዲጂታል ኢንዱስትሪ አውትሶርስ ተደርገው ለሚሰሩ ሥራዎች ኢትዮጵያ ምቹ ሁኔታ ያላት ሀገር መሆኗንም አንስተዋል፡፡ በመድረኩ የዘርፉ ዕድሎችና ተግዳሮቶች በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከዩንቨርስቲ፣ ከአይሲቲ ፓርካ እና በዘርፉ ስኬታማ ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top