መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ
የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሆነ ሥርዓትን በመጠቀም በተበታተነ መልኩ ሲሰጡ የነበሩ 170 በላይ የመንግስት አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜ እና በቅልጥፍና እና ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የተቋቋመ ማዕከል ነው፡፡
በማዕከሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ በበበርካታ ሚኒስቴር መ/ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በማዕከሉ እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡
በፌዴራል ደረጃ የተጀመረውን ይህን አገልግሎት ወደ በክልሎችም ተግባራዊ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ህንፃ ግንባታ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ጊዜና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት አሰጣጥ በአንድ ጣሪያ ስር ተደራሽ በማድረግ ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚቀርፍ በመሆኑ ለውጤታማነቱ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በክልሉ መንግስት አቅጣጫ ተቀምጦ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ መግለፃቸውን የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ዘገባ ያመለክታል፡፡
ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር