Mols.gov.et

“መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡“

January 19, 2024
“መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡“ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የ2024 ግሎባል የአፍሪካ የስታርትአፕ ሽልማት መድረክን በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት መርሃ ግብሩን ከሚያዘጋጀው ግሎባል ኢኖቬሽን ኢንሸየቲቭ ግሩፕ ጋር ነው የተፈራረመው፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልክዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ሃሳብ ማመንጨት የሚችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ያሉባት አገር መሆኗን በመጥቀስ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያን አዲስ ገፅ ለዓለም ለመግለጥ የሚያስችል ነው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕሪነርሺፕና ኢኖቬሽን ምህዳርን ለማስፋት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃ፡፡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንና የፋይናንስ ተቋማትን በአንድ ላይ በማሰባሰብ በተፈጠረው ኔስት (NEST) በተሰኘው ስርዓት አማካኝነት ለኢንተርፕሪነሮች ምቹ መደላድል ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛል ብለዋል ክብርት ሚንስትሯ፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ መልክ ለኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት የሰጠችው ትኩረት የአፍሪካ ስታርታፕ የሽልማት መድረክን ለማዘጋጀት እንዳስመረጣትም ነው ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የገለጹት፡፡ ከዚህ መልካም አጋጣሚ በርካታ ስታርታፕ ቢዝነሶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባው የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአህጉርና ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ላይ ቀርበው ተሸላሚ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሞክሯቸውን ለመሰል ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እንዲያካፍሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top