Mols.gov.et

መርሃ-ግብሩ ተቋማዊ ቅንጅት በማሳደግ ለአዳዲስ ሥራ ፈጠራና ጀማሪ ቢዝነሶች ምቹ ሥነ-ምህዳር መፍጠር የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

October 23, 2023
በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በፈጠራና ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰማሩ አካላት ተቋማዊ ቅንጅት ፈጥረው ለአዳዲስ ሥራ ፈጠራና ጀማሪ ቢዝነሶች ምቹ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር በጋራ የሚሰሩበት መርሃ ግብር ነገ በይፋ ይጀምራል፡፡ መርሃ ግብሩ ሀገር አቀፍ የጀማሪ ቢዝነሶች ኢንሼቲቭ (The Next Ethiopian StartUp Initiative -NEST) የሚሰኝ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ያዘጋጀውና በዘርፉ የተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላትን ወደ አንድ በማምጣት ጠንካራ ተቋማዊ ጥምረት መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል፡፡ መድረኩ ጀማሪ ቢዝነሶች ከክህሎት ልማት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና የወጣቶች ተሳትፎ ጋር በማጣመር እንደ ሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት አስቻይ መደላድልን ለመፍጠር እንደሚያስችልም ነው ክብርት ሚኒስትር የገለጹት፡፡
en_USEN
Scroll to Top