Mols.gov.et

ለጀርመን የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ምላሽ በመስጠት እና…

January 31, 2024
ለጀርመን የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት ምላሽ በመስጠት እና ሀገሪቱ አሁን ለደረሰችበት ኢኮኖሚያዊ ስኬት ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው የሚነገርለት የፌደራል የሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር እና የምርምር ሃላፊ ከሆኑት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሽዋርትዝ እና የኢንስቲትዩቱ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል፡፡ በውይይቱ በሀገሪቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ የምርምርና የልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተመልክተናል። ከዚህ ባለፈ የጀርመን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ በስኬታማነት ከሚጠቀሱት መካከል ግንባር ቀደሙ እንዲሆን ማስቻሉንና በዘርፉ ያካበቱትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠውልናል። በጀርመን የፌደራል የሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኢንስቲትዩት (bibb) ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስርዓት ውስጥ ያካበታችሁትን ልምድና ተሞክሮ ለማካፈል ላሳያችሁን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
en_USEN
Scroll to Top