Mols.gov.et

ለዓለም ባንክ ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ለሆኑት ሚ/ር ኦስማን ዲዮኔ

April 19, 2024
የዓለም ባንክ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዙሪያ ሚንስቴር መስሪያ ቤታችን የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመደገፍ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል:: ለዚህም የባንኩ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ውጤታማ አመራር ሲሰጡና ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሚ/ር ኦስማን ዲዮኔ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነበር፡፡ ሚ/ር ኦስማን ዲዮኔ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ ለምንሰራው ሥራ፤ እንደ ሀገር ደግሞ በተለያዩ ዘርፎች የተቀመጡ የልማት ግቦቻችን እንዲሳኩ ለሰጡት ቁርጠኛ አመራርና ከፍተኛ ድጋፍ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳቸው! ቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው ስኬታማ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ! ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Scroll to Top