ለሴት ካውንስል አባላት የአመራርነት ሥልጠና ተሰጠ
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ የተዘጋጀና በዘመናዊና ውጤታማ የአመራር ስልቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሴት አመራሮች ተሰጥቷል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት የሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መከለያ ባርጊቾ፤ ስልጠናው ሴት አመራሮች ራሳቸውን ለማብቃትና እርስበርስ ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዘርፈ ብዙ ተልዕኮዎችን የሚፈፅም ሚኒስቴር መ/ቤት እንደመሆኑ የሴት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት የሚሰሩ ሥራዎች አገራዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የገለፁት ወ/ሮ መከለያ መሰል መድረኮችን ማጠናከርና ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል፡፡
መሰል የአቅም ማጎልበቻ መድረኮች ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት በቋሚነት ለማስቀጠል እንደሚሰራም የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሃንስ ገልፀዋል፡፡