ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
January 6, 2025

ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስታወቁ፡፡
ክብርት ሚኒስትር ይህን ያስታወቁት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡
የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ስርዓቱ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ አንስቶ በስርዓቱ ላይ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ፈፃሚዎች እንዲሁም ተጠቃሚዎች ግልጽነት እንዲኖራቸው እየተደረገ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መንግስት ከመንግስት፣ መንግስት ከኩባንያ እና ኩባንያ ከኩባንያ ጋር በሚያደርጉት ስምምነት ሊተገበር እንደሚችል ያነሱት ክብርት ሚኒስትር አልፎ አልፎ በግል ጥረት የሚገኙ የሥራ ዕድሎችንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊ በሆነ መንገድ ሥምሪት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ሆኖም በየትኛውም አማራጭ ቢሆን ለሥራ ወደ ውጪ የሚሄዱ ዜጎች የሚስተናገዱት በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ብቻ እንደሆነም በአንክሮት አንስተዋል፡፡
የሁለትዮሽ ስምምነት ከተደረሰባቸው ሀገራት ውጪ ዜጎችን ለሥራ እንልካለን የሚሉ አጭበርባሪዎች መኖራቸውን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ህብረተሰቡ እራሱን ከእነዚህ አካላት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
