Mols.gov.et

ለሁለት ቀን የሚቆይ የሥራ ቅጥር አወደ ርዕይ ተከፈተ

August 31, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት መካካል አንዱ የሆነው ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከነሐሴ 24- 25/2015 ዓ.ም የሚቆይ የሁለት ቀን የሥራ አውደ ርዕይ ከተለያዩ ስመጥር ሆቴሎች ጋር በመተባባር አዘጋጅቷል፡፡ የሥራ አውደ ርዕዩን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና በአዲስ አበባ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በከብርት ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) የከፈቱት ሲሆን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ሃላፈዎችና ተጋባዥ እንግዶች አውደ ርዕዩን ተዘዋውረው ተመልከተዋል፡፡ በሆቴልና ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ በኩል ከፍተኛ ፍላጎት በመኖሩ የኢኒስቲቲዩቱ ተመራቂዎችና እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎችን ከቀጣሪዎችቸው ጋር የሚገናኙበትን መድረክ ለማመቻቸት ዓውደ ርዕዩ መዘጋጀቱን በኢትዮጵያ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ተናግረዋል፡፡ ኢኒስቲቲዩቱ ከባለሙያዎች ማህበራት ጋርም አብሮ እየሰራ እንደሚገኝ የሚናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ እያንዳንዱ ሆቴል በአማካኝ በተለያዩ የሥራ ደረጃዎች እስከ 30 የሚደርሱ ምሩቃንን ይቀጥራል ብለዋል፡፡ በቀጣይ የረጅምና አጫጭር እንዲሁም ተፈላጊ የሆኑ ሰልጠናዎችን መስጠት ከቻልን ገበያው የሚፈልገውን የስው ኃይል በማቅረብና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ማሟላት እንደሚቻል መገንዘባቸውንም አክለው አብራርተዋል፡፡ በዝግጀቱ ላይ ተገኘተው ሥራ ፈላጊዎችን ለመቅጠር ሲመዘግቡ የነበሩ ሆቴሎችም በበኩላቸው ይህ አይነቱ መድረክ መዘጋጀቱ ያለብንን የሰው ኃይል ክፍተት ለመሙላት በእጅጉ ይረዳናል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top