Mols.gov.et

እውቅናው ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የያዘችው የከፍታ ጉዞ የሚያሳኩ ሰልጣኞችን በጥራት ለማፍራት፣ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

September 18, 2025
እውቅናው ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የያዘችው የከፍታ ጉዞ የሚያሳኩ ሰልጣኞችን በጥራት ለማፍራት፣ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት ሥራ አመራር ሥርዓት 21001፡2018 እውቅና አግኝቷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት ሥራ አመራር ሥርዓት 21001፡2018 ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የያዘችው የከፍታ ጉዞ የሚያሳኩ ሰልጣኞችን በጥራት ለማፍራት እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርለታል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴሩን ጨምሮ 16 ተጠሪ ተቋማት እና የስልጠና ኮሌጆች በዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርት መሰረት ሥራቸውን መከወን የሚያስችላቸው የሰርተፍኬት ባለቤት መሆናቸውን የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር ይህም በዘርፉ ዘመን ተሻጋሪ ስራ ለመስራት እና አገልግሎቶችን ያለ ልዩነት በጥራት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ጥራት ያለው ስልጠና መስጠት የሚያስችለው የማሰልጠኛ ክፍሎች እና መሰረተ ልማቶች ማሟላቱን ጠቁመው የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ተልዕኮ ይበልጥ መወጣት እንዲችል ተጨማሪ የማስፋፍያ ግንባታ በቅርቡ ይጀምራል ብለዋል፡፡ ሰርተፍኬቱ የጥራት ስራ አመራር ትግባራ ጅማሮ እንጂ መጨረሻ ባለመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ወደኃላ መመለስም ይሁን መዘናጋት እንደ ማይፈቀድ አስገንዝበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top