ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ገለልተኛ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ላይ ያተኮረ ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያ ካሚል እንደገለጹት ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ገለልተኛ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
አክለውም መንግስት ከስርዓት ጋር የማይለዋወጥ ሲቪል ሰርቪሱ ለመገንባት በቁርጠኛነት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫውን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ውጤታማና ጠንካራ የሆነ የሲቪል ሰርስ መዋቅር ለመገንባት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡