Mols.gov.et

የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ቅንጅት..

February 18, 2026
የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ቅንጅት፤ ለተወዳዳሪ የሰው ኃይል ልማት! ትውልድን ለመጪው ዘመን ማዘጋጀትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ማረጋገጥ የጊዜው አጣዳፊ ጥያቄ ነው። ይህ በተሟላ ደረጃ እውን እንዲሆን በትምህርትና ሥልጠና ተቋማት መካከል ያለው ቅንጅት መጠናከር የሰው ኃይል ልማታችን ከሥራ ገበያው ፍላጎት ጋር እንድናጣጣምና በሥራ ዕድል ፈጠራና በፈጠራ ሥነ-ምህዳሩ ላይ የሚኖረው አበርክቶ እንዲጎለብት ያደርጋል። ላለፈው አንድ ዓመት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን የተቋም በህል ግንባታ ሥራችን አካል የሆነው ወርሃዊ “የማለዳ ውይይት” መርሃ-ግብር በዛሬው እለት በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ እንዲሁም በጥናትና ምርምር ተቋማት መካከል ስትራቴጂካዊና እሴት-አካይ ቅንጅት መፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር ተካሂዷል። ይህ መድረክ ተቋማቱ ለየብቻ ከመጓዝ ወጥተው ለጋራ ሀገራዊ ግብ እንዲሰናሰሉ የሚያስችል አዲስ የትብብር ምዕራፍ ከፍቷል። በዚህም ከእውቀትና ክህሎት ባለፈ፣ ችግርን ወደ ዕድል የሚቀይሩና ሥነ-ልቦናዊ ጥንካሬ ያላቸው፤ በጠንካራ ሥነ-ምግባር የታነጹ፣ አቋራጭ መንገድን የማይሹና ለሀገራዊ ውጤት የሚተጉ፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ የሚያፋጥኑና በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት የሰው ኃይል ልማታችን ዋነኛ ማጠንጠኛ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከምክክሩ ጎን ለጎን የመድረኩ ተሣታፊዎች የኢትዮጵያን የሥራ ገበያ ሥርዓት እና የመንግስት አገልግሎት የፈጠራና የማሻሻያ ማዕከን በመጎብኘት በቀጣይ ተቀናጅቶ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተቀራርቦ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።
tigTIG
Scroll to Top