Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ…

October 12, 2026
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፣ ከቀድሞ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል። በሥራ ርክክቡ ወቅት ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ በዘርፉ የተከነዋኑ ዋና ዋና የትኩረትና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አቅርበዋል። ዘርፉ በእውቀት የሚመራና በትጋት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው፣ ለክቡር አምባሳደር መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል። ክቡር አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር በበኩላቸው፣ ዘርፉ ተቀናጅተን መስራት ከቻልን ለዜጎችና ለሀገር ብዙ የምናተርፍበት ነው ብለዋል። የተጀመሩ የተቋሙን ተልዕኮዎች በተቀናጀ መልኩ ማስቀጠልና የነበሩ ክፍተቶችን ማረም ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልፀዋል።
tigTIG
Scroll to Top