Mols.gov.et

ክፍለ ከተማው በአንድ ጀምበር 1 ሺህ 100 የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ

November 8, 2025
ክፍለ ከተማው በአንድ ጀምበር 1 ሺህ 100 የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “በአንድ ጀምበር 1000 የስራ ዕድል” በሚል መሪ ሀሳብ የአንድ ጀንበር የሥራ ዕድል ፈጣራ ንቅናቄ አካሂዷል፡፡ ንቅናቄው በክፍለ ከተማው ባሉት ሁሉም ወረዳወቀች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ለ1100 ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በንቅ በንቅናቄው መርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ክፍለ ከተማው ባለድርሻ አካላትን አስተባብሮ ለወጣቶች ሥራ ዕድል መፍጠሩ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል። ወጣቶች መንግስት ባመቻቸላቸው የሥራ ዕድል ገቢያቸውን በማሻሻል የራሳቸውና የሀገራቸው ሊለውጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ሀላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው፤ ወጣቶች እውቀታቸውን እና ክህሎታቸውን ተጠቅመው ወደ ሥራ የሚገቡበት ሁኔታ እያመቻቸ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በንቅናቄው ከተፈጠረው 1100 የሥራ ዕድል 61 በመቶ ወጣቶች መሆናቸውን ገልፀው ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ንግድ እና ኮንስትራክሽን የሥራ ዕድሉ የተፈጠረባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
tigTIG
Scroll to Top