Mols.gov.et

“የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማህበራዊ ምክክር መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ…

December 5, 2023
“የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማህበራዊ ምክክር መድረክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራን ክህሎት ሚኒስትር የ2016 ዓ.ም የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ እና ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበት አንድ መቶኛ ዓመት ክብረ በዓል አካል የሆነው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ለፓናል ውይይቱ የመነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአዲሱ የሚኒስትር መ/ቤቱ እሳቤ መሰረት ክህሎት መገንባት ለሚፈለገው የኢንዱስትሪ ሠላምና ምርታማነት ዋንኛውን ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የሥልጠና ሥርዓቱ የገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ እየተቀረፀ እንደሚገኝ ያብራሩት ክብርት ሚኒስትሯ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የኩባንያዎች መፈልፈያ ማዕከላት እንዲሆኑና የአሰለጣጠን ስርዓታቸውን በኢንተርፕሪነርሽፕ እሳቤ ለመቃኘት የሚያስልችሉ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ አገራችን ያላትን ተፈጥሯዊ ፀጋና የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በመቀረጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሰለጣጠን ሥርዓቱ ሀገር ወዳድነትና የሙያ ሥነምግባርንም እንዲያካትት መደረጉን ክብርት ሚኒስትሯ አስታውቀዋል፡፡ ሰልጣኞች ሰው ተኮር (ሶፍት ስኪል) ክህሎት እንዲኖራቸው ማሳቻል፣ የፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግ ትሬዲንግን ማሳደግ፣ የግልና የመንግስት አጋርነትና ማጠናከር፣ ሥራዎችንን ማዘመንና የክህሎትና ቴክኖሎጂ ባንክ ማቋቋም በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸውም በመድረኩ ተብራርቷል፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ እና የሙያ ደህንነት ጤንነት ጉዳዮችን በተመለከተም ምርትና ምርታማነትን ማዕከል ባደረገና አዲስ የኢንዱስትሪ ባህልን ለመገንባትን በሚያስችል መልኩ የዘርፉን እሳቤ ለመቃኘት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት የገለፁ ሲሆን ለዚህም ተግባራዊነት ቋሚ የምክክር መድረክ ማካሄድ የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top