Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን የማዘመን ጉዞ

May 8, 2026
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን የማዘመን ጉዞ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እንደ አዲስ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ እየተገበራቸው በሚገኙ ሰፋፊ የሪፎርም ሥራዎች በርካታ ዜጎች ክብርና ደህንነታቸው ተጠብቆ በውጭ ሀገራት ከሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ። ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አዋጁን ማሻሻል ፣ አዋጁን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ማዘጋጀት ፣ የአስፈፃሚና ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው። በተሻሻለው አዋጅ መሰረት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎችን እንደ አዲስ የመመዝገብና አሰራራቸውን እንዲያዘምኑ የማገዝ ሥራ እየተሰራም ይገኛል ። በዚሁ መሰረት በደረጃ አንድ የተመዘገቡ ኤጀንሲዎች የቢሮ አደረጃጀታቸውን እና የአገልግሎት አሠጣጣቸውን በሚጠበቀው ደረጃ እያዘመኑ እንደሚገኙ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል ።
tigTIG
Scroll to Top