Mols.gov.et

በክልሉ የ100 ቀን ዕቅድ ውስጥ የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ በንቅናቄ …

January 21, 2026
በክልሉ የ100 ቀን ዕቅድ ውስጥ የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ በንቅናቄ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው – ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢፌደሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ቡድኑ በክልሉ ያደረገውን የድጋፍና ክትትል ሥራን አጠናቆ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት ግብረ-መልስ ሰጥቷል። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት፤ በአፈጻጸም የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና በእትረት የተለዩ ጉዳችን ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ እድል ፈጠራ፣ ከአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንዲሁም ከተቋም ግንባታ አንፃር የቀረቡ ጉዳዮች አፈጻጸም በጥንካሬና እንዴ ተሞክሮ መቅረቡን ጠቁመው በቀጣይም የሚደረግ አሰፈላጊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ። ክልሉ የዜጎችን ኑሮን ለማሻሻል የ100 ቀን እቅድ አቅዶ በትኩረትና በንቅናቄ የሚመሩትን ተግባራት በመለየት ወደ ሰራ መግባቱን ጠቅሰው በትኩረትና በንቅናቄ እንዲመራ አቅጣጫ ከተቀመጠባቸው ተግባራት መካከል የሥራና ክህሎት ቢሮ ተግባራት ውስጥ የክህሎት ልማትና የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች መሆናቸውን ገልጸዋል ። በሱፐርቪዥን ቡድኑ የቀረበውን ግብአት መነሻ በማድረግ ልዩ እቅድ በማዘጋጀት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በበኩላቸው፤ በክልሉ በነበራቸው የአጭር ጊዜ ቆይታ በክልሉ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንና እንደተሞክሮ መቀመር ያለባቸው አፈጻጸሞች ተለይተው መያዛቸውን ተጠቁመዋል። መረጃው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው
tigTIG
Scroll to Top