Mols.gov.et

ችግር ለመፍታት፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…

November 30, 2024
ችግር ለመፍታት፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ… በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በጋራ መፍታትን፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻልን እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ታሳቢ በማድረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን የሚያደርገውን የመስክ ምልከታ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ቡድኑ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች ከሪፖርት ባሻገር ያሉበትን የአፈፃፀም ሁኔታ በመመልከት ችግሮችን መፍታትና አፈፃፀሙን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡ በዚህም ቡድኑ ከክልል፣ ከከተማ አስተዳድርና ከየወረዳው አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የተመረጡ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን እና የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን በመመልከት ላይ ነው፡፡
tigTIG
Scroll to Top