Mols.gov.et

የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ ዋናኛ ተልዕኳችን ነው! ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር

November 1, 2024
የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ ዋናኛ ተልዕኳችን ነው! ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የሥራ ዕድልን ማስፋት ለሰላማችን መረጋገጥ እና ለሀገራዊ ማንሰራራት መሰረት በመሆኑ የመንግስት ዋናኛ ተልዕኮ እንደሆነ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪ አየሰጡ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በ2017 በጀት ዓመት 4.3 ሚሊዮን ሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየጠነከረ መምጣቱን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራው ብዙ ዘርፎችንም ጭምር እያካተተ የሚገኝ መሆኑና የልማት እንቅስቃሴ እያደገ የሚሄድ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ዕቅዱ መያዙንም አብራርተዋል፡፡ በግብርና 39 በመቶ፣ በአገልግሎት 31 በመቶ እንዲሁም በኢንዱስትሪ 29 በመቶ የሥራ ዕድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዲጂታላይዜሽንን ተጠቅሞ እየተገበረ በሚገኘው የሪፎርም ሥራዎች ባለፉት 3 ወራት 1መቶ ሺ ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር ለሥራ ማሰማራት መቻሉንም በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ 7መቶ ሺ ሰዎችን በውጭ ሀገር ሥራ ገበያ ላይ ለማሰማራት ዕቅድ መያዙን በማንሳትም በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ወደ አውሮፓ ሀገራትም ጭምር በማስፋት ክህሎት ያላቸው ባለሙያዎች መላክ መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡ በውጭ ሀገራት በሚፈጠሩ የርቀት የሥራ ዕድሎች (outsourcing) ቁጥራቸው ከ26ሺ የሚልቁ ወጣቶች በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም አስረድተዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top