Mols.gov.et

የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 25, 2024
የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶችና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ማሰልጠን ፣ መሸለምና ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ የብሩህ -ኢትዮጵያ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በይፋ አስጀምሯል፡፡ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፤ የምንገነባው ኢኮኖሚ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ኢንተርፕሪነሮችን በስፋት ይፈልጋል፡፡ በውድድሩ ከመላ ኢትዮጵያ በየደረጃው በተካሄዱ ውድድሮች አሸናፊ የሆኑ 150 ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ተወዳዳሪዎቹ የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናቸው ብለዋል፡፡ የብሩህ የንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር በየዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትሯ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮም የውድድሩን ተደራሽነት በመላ ኢትዮጵያ የማስፋት ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ የንግድ ፈጠራ ሃሳብን ጨምሮ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባካሄዳቸው የተለያዩ ውድድሮች ላይ አሸናፊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎች ወደ ምርት ገብተው የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈቱ የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም ዕውን መደረጉንም ክብርት ሚኒስትር አስታውቀዋል፡፡ ከ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በልዩ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሃሳቦች ማበልፀጊያ መርሃ ግብር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶችንና ቴክኖሎጂስቶችን በአንድ ማዕከል በማሰባስብ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን የማሻሻል ብሎም ቴክኖሎጂዎቻቸውን ወደ ሰፊ ምርት የማስገባት ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም አስረድተዋል፡፡ በፕሮግራሙ አንድ ዓመት ቆይታ አዳዲስ ተሞክሮዎች የተገኙበትና የሥራ ፈጣሪዎቾች ሃሳብ ወደ ፍሬ የተቀየረበት እንደነበረም ክብርት ሚኒስትር አመላክተዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top