Mols.gov.et

በዓለም የሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆንና ገበያ ውስጥ ለመቆየት ጊዜውን የዋጀ የሕግ ማዕቀፍ ወሳኝ ነው፡፡

June 24, 2024
በዓለም የሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለመሆንና ገበያ ውስጥ ለመቆየት ጊዜውን የዋጀ የሕግ ማዕቀፍ ወሳኝ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅን ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት መድረክ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልና የአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል አስፈፃሚ እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስርዓቱን ለማሻሻልና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ባረጋገጥ መልኩ እንዲከናወን የተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት አስገኝቷል ብለዋል፡፡ በዓለም የሥራ ገበያ ላይ መወዳደር ብቻ ሳይሆን ገበያ ውስጥ መቆየት ወሳኝ በመሆኑ ተለዋዋጭ የሆነውን ዓለማዊ ሁኔታ ባገናዘበና በሥራ ሂደት የታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት በማረም በዘርፉ ማነቆ የሆኑ የአሰራርና የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል በማስፈለጉ መድረኩ የተዘጋጀ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ አዋጁን ለማሻሻል በርካታ መነሻ ምክንያቶች እንዳሉት ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር በዘርፉ ተግባራዊ ከተደረጉ የእሳቤ ለውጦች ባሻገር የዜጎችን መብት፣ ደህንነትንና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ ብልሹ አሰራሮችን መከላከል እንዲሁም በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ማቃለል ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top