Mols.gov.et

24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር

August 27, 2024
24 ሺህ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ነገ ይጀመራል፡- የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ****************** ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ 24 ሺህ ገደማ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የስራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡ የዘመኑ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን እውቀትና ክህሎት የተላበሱ ባለሙያዎችን ከማፍራት አኳያ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት ሚንስትሯ ገልፀዋል፡፡ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ሙፈሪሃት፤ የሥልጠና ጥራትንና አግባብነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ዘርፉ ለሀገራዊ የብልጽግ ጉዞ የሚጫወተውን ሚና ለማላቅ ያለመ መሰረት ሰፊ ሪፎርም ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ “በዘርፉ ያሉን አሰልጣኝ መምህራን የኢንዱስትሪው አማካሪ፣ አስተባባሪ እና ባለሙያም ጭምር በመሆናቸው በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር መካከል ያለውን ክፍተት ከመሙላት ባሻገር የየአካባቢውን ችግር ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ረገድ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው” ብለዋል፡፡ የአሰልጣኞች መድረክ ዓላማ ግንዛቤን ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን በማሳደግ ለላቀ ውጤት እንዲዘጋጁ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡ ከነሃሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው መድረክ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ አሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃትና በትጋት እንዲከታተሉ የስራና ክህሎት ሚንስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top