Mols.gov.et

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት እና የብራዚል..

April 7, 2026
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት እና የብራዚል-ኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት ስትራቴጂያዊ አጋርነት መሰረቱ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የኢንዱስትሪ ክህሎት ክፍተቶችን በዓለም አቀፍ ትብብር ለመሙላት ከብራዚል ከፍተኛ ተወካዮች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቀ። ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለተሟላ አጋርነትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ተመላክቷል። የብራዚል የክብር ቆንስላ ክቡር ልዊዝ ፈርናንዶ ዳ ሮቻ እና የብራዚል-ኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሮናልዶ ፔሬራ ባሬቶን ያካተተው ልዑካን ቡድን፤የኢንስቲትዩቱን የሥራ ማዕቀፍ፣ ስኬቶችንና በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ዘርፎች ላይ ከኢኒስቲትዩቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቢሩክ የልዑካን ቡድኑ ላሳየው ንቁ ተሳትፎ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ የቀረቡትን የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ዶክተር ሮናልዶ ባሬቶ በበኩላቸው፣ በብራዚልና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቆየ ትብብር መሠረት በማድረግ፣ በሥልጠና የታገዘ የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማምጣት ዘላቂ የሰው ኃይል ልማትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል። በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚፈረመው የመግባቢያ ሰነድ (MoU) የሚከተሉትን ስልታዊ የትብብር መስኮች ያካተተ ይሆናል፦ ስምምነቱ በዋነኛነት ለኢትዮጵያ አሰልጣኞች የ”አሰልጣኞች ሥልጠና” ለማስጠት፣ ሁለትዮሽ ቴክኒካል የልምድ ልውውጦችን፣ አጭር ጊዜ የኢንዱስትሪ ሥልጠናዎችና የፒኤችዲ (PhD) ፕሮግራሞች፣ የጋራ ሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትን የሚመለከቱ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ በዚህ አጋርነት ስድስት ቅድሚያ የሚሰጣቸው የሥልጠና ዘርፎች የተለዩ ሲሆን፤ እነሱም ሜካኒካል ጥገና፣ የኢንዱስትሪ መሣሪያዎችና ማሽነሪዎች፣ የነዳጅና ጋዝ፣ ማዕድንና ማቀነባበር፣ ኤሌክትሪካልና ኦቶሜሽን ሲስተም እንዲሁም ብየዳና ፋብሪኬሽን ናቸው።
tigTIG
Scroll to Top