Mols.gov.et

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2017 ሥራ ላይ ያዋለውን ቤተ ሙከራ (public sector innovation lab) ጎበኙ

September 26, 2025
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2017 ሥራ ላይ ያዋለውን ቤተ ሙከራ (public sector innovation lab) ጎበኙ በጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሳርላህ አብዱላሂ የተመራ የልዑካን ቡድን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጎበኘ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ማሻሻያውን እንዲተገብሩ ከተመረጡት ስምንት የፌዴራል ተቋማት መካከል ወደቀጣይ ምዕራፍ ከተሸጋገሩ ጥቂት ተቋማት አንዱ ነው። ከአገልግሎት አሰጣጥና አስተደዳደር ማሻሻያው በተጨማሪ ዜጋ ተኮር የሆኑ አገልግሎቶች ተቋማዊ ሆነውና ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተሸሻሉ እንዲሄዱ የዓለም አቀፉን የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን በመተግበር በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ የእውቅና ማረጋገጫ ያገኘ የመጀመሪያው ለመሆን ችሏል። ሚኒስቴሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በተለመደው አካሄድ ማሳካት እንደማይቻል በመገንዘብ ለቴክኖሎጂ፣ ለፈጠራ እና ለሀሳብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራም ይገኛል። በዚህም ነባር አሰራሮችን በጥልቀት በመፈተሽ ችግር ፈቺ አሰራሮችን ለመንደፍ የሚያስችል ሥራ የሚሠራበት ቤተ ሙከራ (public sector innovation lab) አቋቁሞ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ ቤተ ሙከራው በዘርፉ ክፍተት ያለባቸውን አሰራሮችን ፈጠራና ፍጥነትን ባማከለ መልኩ የሚያሻሽሉ አዳዲስና ዕሴት አካይ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነው። በጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሳርላህ አብዱላሂ የተመራው የልዑካን ቡድንም በአይነቱ ልዩ የሆነውን ይህን ቤተ ሙከራ (public sector innovation lab) ጎብኝቷል። በጉብኝቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካና የኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሰን ተገኝተው ተሞክሮውን አካፍለዋል።
tigTIG
Scroll to Top