Mols.gov.et

የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ …

December 17, 2025
የአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ ቢሆንም አሁንም አሠራራችንን መፈተሽ እና ከሚመለከተው አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ይጠበቅብናል ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የአካል ጉዳተኞች፣ የህጻናት፣ የፀረ ፆታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን) እና የአለም የኤድስ ቀንን በጥምረት አክብረዋል፡፡ በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ዕለቶቹን አስመልክቶ በሚተላለፉት መልዕክቶች ግንዛቤን ከመጨበጥ ባሻገር የዕለት ተዕለት ህይወታችን አካል ማድረግ እና የአስተሳሰብ ለውጥ ማስፈን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማት እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት እያደገ የመጣ ቢሆንም አሁንም ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቁ ጉዳዮች በመኖራቸው አሠራራችንን መፈተሸ እና ከሚመለከተው ተቋም ጋራም ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡ የክህሎት ልማት ሥራችን አካል ጉዳተኞችን በሚጠበቀው ደረጃ ማካተት እንዲችል ሥርዓተ ስልጠናችንን መፈተሽ፣ ምቹ የማሰልጠኛ መርጃ መሳሪያዎችን በተገቢው መልኩ ማደራጀትና ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመድረኩ አካል ጉዳተኝነትንና ኤች አይቪ ኤድስን አስመልክቶ ከአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽንና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
tigTIG
Scroll to Top