Mols.gov.et

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ

August 24, 2024
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከስልጠና ባለፈ ተልዕኳቸው ተጨባጭ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በምህንድስና ልህቀት ማዕከል እየተሰሩ ያሉ የውጭ ምርት መተካት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ያሉበትን ደረጃ እንዲሁም ሚኒስቴሩ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ላስገነባቸው ቤቶች የሚሆኑ የቤት ቁሳቁሶች ዝግጅትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ በዚህም ሥራው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ክብርት ሚኒስትር በዘርፉ የተደረገው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ያመጣውን ውጤት ማሳያም እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከሥልጠና ባለፈው ተልዕኳቸው የሥልጠና ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው የአካባቢያቸውን ችግር እየፈቱ የውስጥ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እና የውጭ ምርቶችን ሊተኩ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን እየሰሩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ መደረጉንም ክብርት ሚነስትር አንስተዋል፡፡ ይህም ተጨባጭ ውጤት እየተገኘበት ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር በክረምት በጎ ፈቃድ ለተገነቡት ቤቶች የሚሆኑ ግብዓቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት እያመረቱ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top