Mols.gov.et

የሥራ ስምሪቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል።

August 14, 2024
የሥራ ስምሪቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርጋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከሳውዲ አረቢያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ልዑኩ በታካሞል ሆልዲንግ የሙሳነድ ፖርትፎሊዮ ዋና ስራ አስፈፃሚ ካሊድ አልቱኪ የተመራ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፤ በዘርፉ የተደረገው ሪፎርም መነሻና መዳረሻው የዜጎችንን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ በመሆኑም በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ዜጎች በቂ ስልጠና እንዲወስዱና ብቃታቸውን በምዘና እንዲያረጋግጡ እየተደረገ ነው። አገልግሎቱ ፍትሃዊና ቀልጣፋ እንዲሆን የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሰርዓቱን ለማዘመን እና ህገወጥነትን ለመከላከል የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል። የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸው እስከ አሁን ባለው ኢትዮጵያ በፍጥነትና በተሻለ የጥራት ደረጃ የሰው ሀይል በማሰማራት ቀዳሚ መሆኗን ገልፀው ባዩት የሪፎርም ሥራ እጅግ መደነቃቸውንና መደሰታቸውን ገልፀዋል። በዘርፉ ተግባራዊ የተደረገው ሪፎርም ውጤታማ እንደሆነ የጠቆሙት የልዑካን ቡድኑ በዘርፉ ባለው የሁለቱ ሀገራት ትብብርም ደስተኛ እንደሆኑና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
tigTIG
Scroll to Top