የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት፤ ለምርታማነት!
November 17, 2025
የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት፤ ለምርታማነት!
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠ ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ውጤታማ በማድረግ ለሀገራዊ የልማት ፍጎት በቂ ምላሽ መስጠት እንዲችል መሠረተ ሰፊ የሪፎም ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
በዘርፉ ተለይተው ወደ ሥራ ከገቡ 11 አዳዲስ እሳቤዎች መካል የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት አንዱና ዋነኛው ነው።
ይህ እሳቤ ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ መስጠትን፣ የየአካባቢውን ፀጋዎችን በአግባቡ ማልማትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማላቅን፣ የሥራ አጥነትን ምጣኔን ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስን እና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ደረጃና ምርታማነትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻልን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
በዚህ አደረጃጀት ስምንት ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዞኖች ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተቋማት የየአካባቢያቸውን የመልማት ፀጋን እና አንፃራዊ ጠቀሜታን መሰረት አድርገው ስልጠና እንዲሰጡ ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ይህም የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገው የክህሎት ልማት አቅጣጫ ማዕቀፍ የሚመራ ነው፡፡
ለምሳሌ በአዋሳና አካባቢዋ የሚገኙ ተቋማት በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማትና እሴት በማከል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነለት በሚያልቁ፣ በአካባቢው ለሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና የሰለጠነ የሰው ሀይል አቅራቢ በሚያደርጋቸው እንዲሁም አካባቢያዊ የልማት ፀጋን መሰረት በማድረግ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር በሚችሉ የስልጠና መስኮች ላይ እንዲያተኩሩና በዛው መስክ የልህቀት ማዕከል እንዲሆኑ የሚያበረታታ ነው፡፡
በዚህ ባህሪውም ዘርፉን ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶች ምላሽ ሰጪ እንዲሆን ለማድረግ ከተቀረፁ አዳዲስ እሳቤዎች መካከል ጠንካራ አመራርና ውሳኔ ሰጭነትን ከሚፈልጉት ሥራዎች መካከል ዋናው ነው ማለት ይቻላል፡፡
ባለፉት ዓመት የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀትን ጨምሮ በዘርፉ የተለዩ የሪፎርም እሳቤዎችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች መሬት ለማስነካት ሰፊ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችንም ማየት ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀት ስትራቴጂን ለመተግበር ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡
በዚህም ተቋማት በአካባቢያዊ የመልማት ጸጋ ልየታ መሰረት የስልጠና ዘርፋቸው በመዘጋቱ ወደሌላ ተቋማት የተዛወሩ አሰልጣኞችን የመቀበልና በምስጋና የመሸኘት ሥራ ጀምረዋል፡፡
የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም ከተቋሙ ወደ ሌላ ቦታ ለተዛወሩ የሽኝት እንዲሁም ወደ ተቋሙ ለመጡ አዳዲስ አሰልጣኞች ደግሞ የአቀባበል መርሃ ግብር አዘግጅቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በዚህም በተቋሙ አንፃራዊ የልማት አቅም ልየት መሰረት 136 አሰልጣኞች ወደ ሌላ ተቋም የተዛወሩ ሲሆን 55 የሚሆኑ አዳዲስ አሰልጣኞችን የተቀበሉ መሆኑን የጄነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ገልፀዋል፡፡
ለዕድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑን ያነሱት አቶ መለሰ ከተቋሙ ለተሸኙ አሰልጣኞች የምስጋና፤ ተቋሙን ለተቀላቀሉ ደግሞ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በኮሌጁ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና አሁን ላይ በጡረታ ለተሰናበቱ ባለውለታዎች፣ በ2017 ዓ.ም ምርጥ ቴክኖሎጂ ለሰሩ አሰልጣኞች እንዲሁም ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምር ላደረጉ አሰልጣኞች የሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡



