Mols.gov.et

ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ

August 21, 2024
ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የማኅበረሰብ አቀፍ የሥራ ባህልና ምርታማነት የውይይት የአስተባባሪዎች የጋራ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ በየክልሉ የተካሄዱ የማህበረሰብ አቀፍ ምክክሮችና ውይይቶች ያመጡት ውጤትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በዚህም የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት በሚል መሪ ሀሳብ የአመቻቾች የአሰልጣኞች ስልጠና ወስደው ተግባራዊ ያደረጉ አመቻቾች ውይይቱን ላልጀመሩ ለአማራና ለትግራይ ክልል እንዲሁም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች ተሞክሯቸውን አካፍለዋል፡፡ ውይይቱ በምርታማነት ላይ ተጨባጭ ውጤት የማምጣት አቅም ስላለው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ እና ለዚህም በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ለምክክሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡ የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀመራቸው ሀገራዊ ሪፎርም ሥራዎች አንዱ ሲሆን ውይይቱ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰብ ድረስ በሙያና ሙያተኛ፤ በሥራና ሠራተኝነት እንዲሁም በታታሪነትና ሠርቶ መለወጥ ላይ አውንታዊ እይታ በመፍጠር ምርታማነትን ለማሳደግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
tigTIG
Scroll to Top