Mols.gov.et

እሴት ሰንሰለትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ

June 4, 2026
እሴት ሰንሰለትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ውጤት አምጥቷል በሶማሌ ክልል እሴት ሰንሰለትን (Value-Chain) መሠረት ያደረጉ የሥራ ፈጠራ ተግባራት ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ። የሱማሌ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ ፤ ሥራዎቹ በፌዴራል መንግስት የሥራ ፈጠራ ፖሊሲዎችና የሪፎርም ሃሳቦች መሠረት የተከናወኑ መሆኑን ገልጸው ተግባራቱ የክልሉ መንግስት ለወጣቶች ሥራ ፈጠራና ለአካባቢ ኢኮኖሚ ማነቃቂያ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳዩ መሆኑንም ጠቁመዋል። እንደ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ ማብራሪያ፣ የገበያ ተኮር የልማት አቅጣጫን መሠረት ያደረገው ይህ ፕሮግራም በጅግጅጋና በጎዴ ከተሞች በሙከራ ደረጃ ተተግብሯል። ፕሮግራሙ በወተት፣ በእንቁላል፣ በሽንኩርትና በሥጋ ምርቶች አቅርቦት ላይ ትኩረት አድርጎ ተሰርቷል። በሂደቱ 28 አቅራቢዎች (Supply Side) እና 22 ፈላጊዎች (Demand Side) በማስተሳሰር ከ2,200 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት በትስስሩ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ አሰራር የአካባቢውን የምርት አቅርቦት ሥርዓት እና የገበያ ትስስር በእጅጉ ከማሻሻሉም በላይ ለአምራቾች አስተማማኝ ገቢ መፍጠሩንና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደጉን ገልጸዋል። ሂደቱም ክልሉ ወደ ዘላቂና ገበያ-ተኮር የሥራ ፈጠራ ሥርዓት እየተሸጋገረ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
tigTIG
Scroll to Top