Mols.gov.et

ኢንስቲትዩቱ በቀጣናው ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ

February 5, 2026
ኢንስቲትዩቱ በቀጣናው ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት (FTVTI) ከሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የትምህርት፣ ባህልና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር ይፋዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎችን ለሶማሊያውያን ወጣቶች ደረጃውን የጠበቀና ጊዜውን የዋጀ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡ ስምምነቱን የፈረሙት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ሀፍቶም ገብረእግዚአብሔር እና የሶማሊያ ትምህርት ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ሀሰን ናቸው። በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ረዳት ፕሮፌሰር ሀፍቶም እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በቀጣናው ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ደረጃ ለማሻሻል ለሰልጣኞችና ለአሰልጣኞች ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ እንደ ትልቅ ምዕራፍ በሚቆጠረው በዚህ ስምምነት መሰረት፤ ኢንስቲትዩቱ ለ25 ሶማሊያውያን ተማሪዎች የቅድመ-ምረቃ (Bachelor’s degree) የነፃ ትምህርት ዕድል ሰጥቷል። ይህም ኢንስቲትዩቱ ለጎረቤት ሀገራት የላቀ የስልጠና እድሎችን ተደራሽ ለማድረግ የያዘው ተልዕኮ አካል መሆኑ ተገልጿል። ረዳት ፕሮፌሰር ሀፍቶም አክለውም፤ ይህ ስምምነት የኢንስቲትዩቱ የቀጣናዊ ትስስር ስትራቴጂ ዋና አካል መሆኑንና የአቅም ግንባታ መርሃ ግብሩም ወደፊት በስፋት እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
tigTIG
Scroll to Top