Mols.gov.et

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ሙሉ አባል ሆነች

August 10, 2024
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት ሙሉ አባል ሆነች ይህን አስመልክቶ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትር በመግለጫቸው ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት የአባልነት ጥያቄ አቅርባ ላለፉት ሁለት አመታት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ምላሹን ስትጠባበቅ ቆይታለች፡፡ የድርጅቱ ቦርድ ሰሞኑን ባሳለፈው ውሳኔ ኢትዮጵያ የድርጅቱ 88ኛ ሙሉ አባል ሆናለች ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ እንዳለው አመልክተው ሀገራችን በክህሎት ልማት ከተቀረው ዓለም አኳያ ያለችበትን ደረጃ ማየት የሚያስችልና ልምድና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ምቹ ምህዳርን የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በየሁለት ዓመቱ በኦሎምፒክ መልክ የሚካሄድ የዓለም የክህሎት ወድድር መኖሩን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በዚህ መድረክ ዓለም አቀፍ ልምዶች የሚቀሰሙበት፣ የኢንዱስትሪ ትስስር የሚፈጠርበት እና የክህሎት ሽግግር የሚደርግበት በመሆኑ የተሻሉ ልምዶችን እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ በመጪው መስከረም ወር ላይ በፈረንሳይ፣ ሊዮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በሶስት የሙያ መስኮች የምትሳተፍ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top