Mols.gov.et

በዲጂታል አሠራር ዙሪያ ለኤጀንሲዎች ሥልጠና ተሰጠ

January 5, 2026
በአዲሱ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅና በዲጂታል አሠራር ዙሪያ ለኤጀንሲዎች ሥልጠና ተሰጠ ‎ ‎በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የውጭ ሀገር አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች ያዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ። ‎ ኤጀንሲዎች ዕውቀትና ክህሎትን መሠረት ያደረገ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሠሩ ማስቻል የስልጠናው ዋንኛ ዓላማ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ‎በውጭ ሀገር ሥምሪት ሥርዓት ውስጥ አስፈላጊና መሟላት የሚገባቸው ሂደቶች ማለትም የሲስተም አጠቃቀም፣ የኤሌክትሮኒክስ ትኬቲንግ (Booking & Re-booking)፣ የሥራ መደቦች የምደባ ሥርዓት(Job Position)፣ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC) ቅሬታ አቀራረብ እና የውልና የQR ኮድ ጥያቄዎችን አፈጻጸም የተመለከቱ የቴክኒክ ሥልጠናዎችም በመርህግብሩ መካተታቸው ተጠቁሟል፡፡ ‎ ‎ወደ ውጭ ሀገር ለሥራ የሚሄዱ ብቻ ሳይሆን የተመላሽ ሠራተኞችን አያያዝ የተመለከቱ ውይይቶችም ተካሂደዋል፡፡ ‎ ‎በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው አዲሱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ዙሪያ ኤጀንሲዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ለሥራው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በተለይም በአዲሱ አዋጅ መሠረት የፈቃድ አሰጣጥ ሂደትና ሌሎች ሕጋዊ መስፈርቶች ላይ ግልጽነት በመፍጠር፣ በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስህተቶችን በጋራ ለመከላከል በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ‎ ‎ይህ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ኤጀንሲዎች ያላቸውን የሲስተም አጠቃቀም ክፍተት በመሙላት፣ የዜጎችን መብትና ደኅንነት ባከበረ መልኩ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
tigTIG
Scroll to Top