በዘርፉ የተጀመረው የአቅም ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር ) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
July 2, 2025

በዘርፉ የተጀመረው የአቅም ግንባታ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር )
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች የአቅም ግንባት ስልጠና ሞጁል ዝግጅት ተጀመረ።
በክህሎት ልማት ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በተጨባጭ ክፍተቶችን የለዩ እና እሴት የሚያክሉ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
በዚህም ለአሰልጣኞች የቴክኒካል ክህሎቶችን ማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ለመስጠት በጥናት ላይ የተመሰረተ የሞጁል ዝግጅት ተጀምሯል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደሀገር የቴክኒክና ሙያ አመራሮችንና አሠልጣኞችን አቅም ለማጎልበት እየተሰራ ነው።
ይህም ክፍተቶችን በሚሞላ፣ ከሥልጠና ጥራትና አግባብነት አኳያ እሴት በሚያክልና ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ (ዶ/ር ) በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ አመራርና አሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸው በተለያየ አግባብ ሲጠና ቆይቷል።
ለዚህ ሞጁል ዝግጅት መነሻ የሚሆኑ የክህሎት ክፍተት መለያ ሰነዶች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መዘጋጀታቸውን የገለጹት ዶ/ር ሀብታሙ እነዚህን መነሻ ያደረገ የስልጠና ሞጁል እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል።







