በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ ያተኮረው ስምምነት
August 6, 2026
በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ ያተኮረው ስምምነት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ከጣሊያኑ ማርኬ ክልል (Marche Region) መንግሥት እና ለአፍሪካ የልማት አጋርነት ከሚሠራው APA-CVM ከተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የ1 ቢሊዮን ብር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የዉጤት ተኮር ሥልጠናና ተቋማት ልማት ዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ ዳግማዊት ግርማ፣ የAPA-CVM የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወካይ ጆናታን አስካኒ (Jonathan Ascani) እንዲሁም የማርኬ ሪጅን የዓለም አቀፍ ትብብር አስተባባሪ አቶ ናታሊኖ ባርቢዚ (Natalino Barbizzi) በይፋ ተፈራርመውታል።
ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚቆየውና በጣሊያን ማርኬ ሪጅን መንግሥት ሙሉ በሙሉ በገንዘብ የሚደገፈው ይህ የልማት ፕሮጀክት፣ በዋነኝነት በሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ላይ አተኩሮ እንደሚንቀሳቀስ ታውቋል።
እነዚህም የቴክኒክና ሙያ (TVET) ተቋማትን አቅም በማጎልበት የሰልጣኞችንና የአሰልጣኞችን የሙያ ክህሎት ማሳደግ፣ ለሥልጠና ተቋማቱ አስፈላጊ የሆኑ ዘመናዊ የመማሪያና የቴክኖሎጂ ግብአቶችን ማሟላት እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶችና ባለሙያዎች የሥራ ዕድልና የገበያ ትስስር ማመቻቸት ናቸው።
መረጃው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው


