Mols.gov.et

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል …

February 22, 2026
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል የዜጎችን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን ተገለፀ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ የተከናወኑ የሥራና ሥራ ሥምሪት፣ የክህሎት ልማት፣ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳዮች እና የተቋም ግንባታ ተግባራትን ላይ ጠለቅ ያለ የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡ የድጋፍና ክትትል ቡድኑን የመሩት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ አዝመራ ከበደ፤ በክልሉ ተሞክሮ የሚወሰድባቸው አበረታች ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል፡፡ በክልሉ በክህሎት ልማት ዘርፍ የተቀረጹ አዳዲስ እሳቤዎች ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አድንቀው በተለይ ኢንተርፕራይዞች ለመደገፍ የሚደረገው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ሥራ፣ በተጨባጭ ውጤት እየታየበት መሆኑ በመስክ ምልከታው መረጋገጡን ጠቁመዋል። ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ከማድረግ ባሻገር በኮሪደር ልማት እና በሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቮች ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተቀረጹ እሳቤዎች ወደ መሬት ለማውረድ የተጀመሩ ጥረቶች አሰሪም ሰራተኛውም ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ ቡድኑ በቆይታው ጠንካራ ጎኖችን ተጠናክረው አንዲቀጥሉ ከማበረታታት ባለፈ፣ በሂደቱ የታዩ ክፍተቶች እንዲታረሙና ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አመላክቷል፡፡ ይህ የድጋፍና ክትትል ሥራ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑና የዜጎችን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ በሚያስችል መንግድ ለመተግበር ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንም የክልሉ የዘርፉ ኃለፊዎች ገልጸዋል።
tigTIG
Scroll to Top