በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን የመስክ ምልከታ እያደረገ ይገኛል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በሀረሪ፣ በማዕከላዊና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም በሸገር ዙሪያ በመንቀሳቀስ ከየክል የሥራ ኃላፊዎቸ ጋር በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ሥራዎች ላይ ውይይት በማድረግ እስከ ታችኛው መዋቅር በመውረድ ሥራዎችን ተመልክቷል፡፡
ቡድኑ በምልከታው ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ተቋም አቅም ግንባታ አኳያ እንደ አቅጣጫ የተቀመጡ ሥራዎችን ያሉበትን ደረጃ የመፈተሸ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ለአፈፃፀም ማነቆ የሆኑ ጉዳችን በመፍታት ለላቀ አፈፃፀም መደላድል መፍጠር አላማው ባደረገው በዚህ የድጋፍና ክትትል ሥራ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማቱ የየዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡