በሀገራችን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በፍጥነት እያደገ የሚገኝ በመሆኑ የብየዳ ሙያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተፈላጊ ነው፡፡ ዶ/ር ብሩክ ከድር የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር
November 11, 2024
በሀገራችን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በፍጥነት እያደገ የሚገኝ በመሆኑ የብየዳ ሙያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተፈላጊ ነው፡፡
ዶ/ር ብሩክ ከድር
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም በሆነው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ስር በሚገኘው የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ዓለም አቀፍ ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የብየዳ ስልጠኞች ተመረቁ፡፡
በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በሀገራችን በፍጥነት እያደገ የሚገኝ በመሆኑ የብየዳ ሙያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተፈላጊ መሆኑን ጠቁመው የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት ጉልህ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ ወርክሾፕ ያለውና በብቁ አሰልጣኞች የተሟላ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ በያጆችን እያፈራ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
‹‹የብየዳ ሰልጣኞች እጃችሁ ላይ ያለው ሙያ እጅግ የከበረ በመሆኑ ልትኮሩበት ይገባል ››ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ‹‹ያገኛችሁትን ሙያ ተጠቅማችህ በተከታታይ ልምምድ ራሳችሁን ካበቃችሁ በሀገር ግንባታ ውስጥ የላቀ ሚና ይኖራችኋል›› የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል በመደበኛ ዘርፍ ከሚሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በሀገራችን ለሚገኙ ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚሰሩ በያጆችን በአጫጭር ጊዜ ስልጠና እያበቃ እእደሚገኝም እና በቀጣይ ማዕከሉን ዘመኑ ከደረሰበት የብየዳ ጥበብ ጋር በሚጣጣም ደረጃ የማዘመን ሥራዎች በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስትትዩት ትብብር እንደሚሰራም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰላሙ ይስሃቅ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሰልጣኞች ዘወትር የተግባር ልምምድ በማድረግ ራሳቸውን እንዲያበቁና የብየዳ ሙያ ጥራትን በሀገራችን ለማረጋገጥ ግዴታቸውን እንዲወጡ መልዕክታውን አስተላልፈዋል፡፡