Mols.gov.et

ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው – ሚኒስቴሩ

October 19, 2025
ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ ነው – ሚኒስቴሩ ስታርታፕ ለስራ ዕድል ፈጠራ እድገት የሚኖረውን አቅም ለመጠቀም ምቹ መደላድል እየተፈጠረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ገለፁ። መንግሥት ስታርታፕን በማሳደግ ኢኮኖሚውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችሉ አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎችን አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰለሞን ሶካ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የስታርታፕ ስነ ምኅዳሩን ማስፋት የሚያስችል የክህሎት ልማትና አዳዲስ የስራ ዕድል ፈጠራን የሚያበረታቱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች የሚወዳደሩበት “ብሩህ ኢትዮጵያ” የክህሎት ውድድር ሀገራዊ ልማትን የሚያሳልጡና ስታርታፖችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ሺህ 350 የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ዜጎች እውቅና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በሀገሪቱ የሚኖረውን ፋይዳ አሟጦ ለመጠቀም አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብ ላላቸው ስታርፖች የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የአቅም ግንባታና ሌሎች ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት፡፡ የዜጎችን የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ስታርታፕ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት፤ ስታርፖች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስታርታፕ ዘርፍ ኃላፊ ሙልጌታ ውቤ በበኩላቸው፤ የወጣቶች የስራ ፈጠራ ዝንባሌ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የስታርታፕ አዋጅ በማጽደቅ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡ የፈጠራ ሀሳቦች ስታርፕ መሆናቸው በህጉ ተለይቶ ምዝገባና ስያሜ ከተጠሰ በኋላ አስፈላጊው የፋይናንስና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡ አዋጁን ገቢራዊ ለማድረግ ሀገር አቀፍ የስታርታፕ ፖርታል እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ የማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል ሰል ኢዚያ ዘግቧል::
tigTIG
Scroll to Top