Mols.gov.et

ምርትና ምርታማነትን ማጎልበት

March 13, 2026
ምርትና ምርታማነትን ማጎልበት፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ማመንጨትና ከባቢያዊ ችግሮችን መፍታት የሚጠበቅባቸው የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ከሥልጠና ማዕከልነት ባለፈ የኩባንያዎች መፈልፈያ፣ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፍለቂያና የሥራ ዕድል ፈጣራ ማዕከላት እንዲሆኑ የሚያስችል አዲስ እሳቤን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ የዚህ እሳቤ ዋንኛ ዓላማ የስልጠና ተቋማቱ ያላቸውን ማሽኖችና ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ከባቢያዊ ችግርን የሚፈቱ ምርቶችን እንዲያመርቱ ፣ በሂደቱም በተግባር በተደገፈ መልኩ ሰልጣኞቻቸውን በክህሎት እንዲያበቁ ማስቻል ነው፡፡ በዚህ መሰረት በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ራሱን የቻለ ህጋዊ ኢንተርፕራይዝ አቋቁመው ወደ ሥራ እየገቡ ይገኛሉ፡፡ የመሰል ኢንተርፕራይዞች መቋቋም ተቋማቱ የውስጣዊ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ፣ ምርትና ምርታማነትን እንዲያጎለብቱና አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በማመንጨት የአካባቢቸውን ችግር እንዲፈቱ የሚያስችል አቅምን እንደሚያላብሳቸው ይጠበቃል፡፡
tigTIG
Scroll to Top