Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

October 6, 2025
ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዓመታዊ የቤተሰብ ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል፡፡ በመርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ተሳትፈዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ሚኒስቴሩ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የሠራተኛው ቤተሰብ ድጋፍ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ በመሆኑም የሥራና ክህለሎት ሚኒስቴር የቤተሰብ ቀን ማክበር የተፈለገው የእርስ በእርስ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር ሠራተኛው ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ቤተሰቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስቴሩ እስካሁን ካሳካቸው ስኬቶች በላይ በቀጣይ ሰፋፊ ስራዎች ከፊት ለፊቱ መኖራቸውን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይም ሠራተኛው ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ ቤተሰቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሚኒስቴሩም ሰራተኛውና ቤተሰቡን ለማገዝ እና ችግሮቻቸውን ለማቅለል የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ በሚኒስቴሩ እና በተጠሪ ተቋማት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን መጎብኘትን ጨምሮ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የሥራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top