Mols.gov.et

ሀገር እርስ በርስ በመተሳሰብና በመደጋገፍ ሂደት ውስጥ ይሰራል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

July 27, 2025
ሀገር እርስ በርስ በመተሳሰብና በመደጋገፍ ሂደት ውስጥ ይሰራል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች በሀረሪ ክልል በአረንጓዴ አሻራና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ችግኝ በመትከል ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ እርስ በርስ በመተሳሰብና በመደጋገፍ ሂደት ሀገር ይሰራል ብለዋል፡፡ አንዱ ስለአንዱ ለማሰብ የግድ ዘመድ መሆን አይጠይቅም፤ ለመተሳሰብ ትልቁ አስተሳሳሪ ገመዳችን ኢትዮጵያዊነት በመሆኑን ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ መሰል ድጋፎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር በበኩላቸው በክረምት በጎ አድራት ሥራ እንደ ሀገር ሰፋፊ የአረጓዴ ልማት ስራዎች እና በርካታ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች ቤት መገንባት፣ የማዕድ ማጋራትና የተማሪ ምገባ የመሳሰሉ ሰፋፊ ስራዎች መሰራቱን ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ እርስ በእርስ የሚያስተሳስሩ በየአካበቢው እያከናወናቸው የሚገኙ የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መሰል ድጋፎች የአብሮነት እና የወል ትርክት የሚያጠነክሩ በመሆኑ ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ሀምሌ 18/2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
tigTIG
Scroll to Top