Mols.gov.et

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር በኢትዮጵያ እና በኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

July 20, 2025
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በማጠናከር በኢትዮጵያ እና በኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሚኒስቴሩ ኤል ጂ ኮይካ ሆፕ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ አቅምና ደረጃውን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት በቅርበት እንደሚያግዝ አስታወቀ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኮሪያ መንግስት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ኮይካ) ካንትሪ ዳይሬክተር ጆ ሀን ዱክ እና በኢትዮጵያ የኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ዳይሬክተር ያንግ ሰንብ ሀውን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይቱ በክህሎት ልማቱ መስክ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በመድረኩ የኤል ጂ ኮይካ ሆፕ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ባለፉት 10 ተከታታይ ዓመታት በአይሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ የስልጠና መስክ ጥራት ያለው ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡ ከሚሰጠው ስልጠና ባሻገርም ሰልጣኞችን ከሥራ ጋር ከማስተሳሰርና አሰልጣኞችን ከማብቃት አኳያም ውጤታማ ሥራዎችን እንዳከናወነም ተመላክቷል፡፡ በቀጣይም ኮሌጁ አቅሙንና ደረጃውን ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ በክህሎት ልማቱ መስክ የኮሪያ መንግስት በኢትዮጵያ ትልቅ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ምስጋና አቀርባለው ብለዋል፡፡ አሁን የተጀመረው ጥረትም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ በኢትዮጵያ እና በኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ከፍ የሚያደርግ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትር የኮሌጁን አቅምና ደረጃ ለማሳደግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኮይካ እና ከኤል ጂ ኤሌክትሮኒክስ ጋር በቅርበት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ የኮሪያ መንግስት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ኮይካ) ካንትሪ ዳይሬክተር ጆ ሀን ዱክ፣ በኢትዮጵያ የኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ዳይሬክተር ያንግ ሰንብ ሀውን እና የሥራ ባልደረቦቻቸው በኤሌክትሮኒክስ እና በአይሲቲ መስክ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እያደረጉ ላለው ጥረትና በትብብር ለመሥራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ክብርት ሚኒስትር ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ሀምሌ 13/2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
tigTIG
Scroll to Top