ዘንድሮ በሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ዕምርታ የታየበት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በዘንድሮ በጀት ዓመት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች 4.5 ሚሊየኝ በላይ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተሩ በማብራሪያቸው ዘንድሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ዕምርታ የታየበት ነው ብለዋል፡፡
በዋናነት በግብርና ዘርፍ 1.8 ሚሊየን ወይም 39 በመቶ ፤ በአገልግሎት ዘርፍ 1.6 ሚሊየን ወይም 35 በመቶ በኢንዱስትሪ ዘርፍ 680 ሺህ ወይም 15 በመቶ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችለዋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛ ቢሆንም ካለው ፍላጎት አኳያ አሁንም ሰፊ ሥራ ይጠይቃል ብለዋል፡፡