Mols.gov.et

በ48ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር

September 30, 2026
በ48ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር የተሳተፈው የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የሙያና ክህሎት መድረክ ወክሎ በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው 48ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ስኬታማ ተሳትፎውን አጠናቆ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ በሚከተሉት ዘጠኝ የሙያ ዘርፎች ተወክላለች፡- 1. Welding 2. Plumbing and Heating 3. Cabinetmaking 4. Bricklaying 5. Electrical Installation 6. Fashion Technology 7. Hairdressing 8. IT Network System Administration 9. Digital Interactive Media Technology በእነዚህ ዘርፎች በተወከሉ 9 ወጣት ተወዳዳሪዎች እና 9 አሰልጣኝ ኤክስፐርቶች አቅሟን በዓለም መድረክ ያሳየች ሲሆን፣ እያደገ የመጣውን ሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ማሳያም ሆነዋል። በዚሁ ውድድር ወጣት ሮቤል ለገሰ በ Digital Interactive Media Technology የላቀ የክህሎት ብቃቱን በማስመስከርና ከኢትዮጵያን ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ የ “Best of Nation Medal” አሸናፊ ለመሆን ብቋል። 🏅 የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎች (Competitors) 1. ሮቤል ሌገሰ (Best of Nation Medal አሸናፊ) 2. አትክልት ታዬ 3. አትክልት ታዬ 4. ታምራት ሻመና 5. እርስቱ አጥናፍ 6. መርድ መረሳ 7. ዮሃንስ መንግስቱ 8. ያዕቆብ ነጋ 9. ቃልኪዳን ፋንታሁን 10. ፈሮን ነጂብ 👥 ኤክስፐርቶች (Technical Experts) 1. ዶ/ር ዮሴፍ ከፍያለው 2. ዶ/ር መርቱ ዋቁማ 3. ማኅሌት ተክላይ 4. ዳንኤል ጌታቸው 5. ፋንታሁን ይማነ 6. ሰሎሞን ጌታሁን 7. ሞቲ ነቢዩ 8. ዳግም ኮስትሬ 9. ተንሳይ ገብረመስቀል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎ ዋና ዓላማ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትን ማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪውን የሥራ ዓለም ፍላጎት የሚያሟላ ብቁ የሰው ሀብት መገንባት እና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የክህሎት ባለቤቶችን ማፍራት ነው። ከተሳትፎው የተገኘው ዓለም አቀፍ የሙያ ስልጠናና ምዘና ሀገራዊ የክህሎት ልማት ምህዳራችንን ለማጠናከር፣ የኢንዱስትሪ ትስስርን ለማስፋት እና ሀገራዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅሞችን ለማሳደግ በከፍተኛ ትኩረት የሚተገበር ይሆናል። ክህሎት የሕይወት መቀየሪያ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እና የሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ዋና ምሰሶ ነው!
tigTIG
Scroll to Top