Mols.gov.et

በግብርና ተቋሞቻችን የሚተገበረው ሪፎርም …

December 15, 2023
በግብርና ተቋሞቻችን የሚተገበረው ሪፎርም በዘርፉ የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተጠቆመ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሀገራዊ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ወሳኝ ነው። ከዚህ አንፃር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የጀመረው ሪፎርም ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ለመገምገም ተችሏል። ሀገራዊ የልማት ዕቅዱ የተሳካ እንዲሆንና ኢኮኖሚያዊ ነፃነታችንን መቀዳጀት እንድንችል ግብናችንን ማዘመንና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተጠሪ የሆኑ የግብርና ተቋማትን በበቂ ጥናት ላይ በመመስረት ሪፎርም የማድረግ ሥራ ተጀምሯል። ከሚኒስትቴር መስሪያ ቤቱና ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጣውና ይህንን ሥራ የሚያስተባብረው አካል የደረሰበትን ደረጃ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርት አቅርቧል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ እንደገለፁት የዚህ ሪፎርም ዋና ዓላማ በተቋማቱ የሚሰጠውን ስልጠና ጥራት ለማረጋገጥ፣ ግብርናውን ለማዘመን እና በሂደቱም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው። ከግብዓት አቅርቦት እሴት እስከታከለበት ምርት ለማቅረብ ያለመና ከስልጠና ጥራት ከማረጋገጥ ባሻገር ተቋማቱ በግብርናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እውን ማድረግ ሌላው ዓላማ መሆኑን ያወሱት ክብርት ሚኒስትር የየአካባቢውን አርሶና አርብቶ አበር ህይወት ማሻሻል እና በሂደቱም ገበያ የማረጋጋት ግብ ያለው መሆኑንም አስረድተዋል።
tigTIG
Scroll to Top